Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ UNDP (United Nations Development Programme)ጋር በመተባበር በ BRIDGE (Building Resources in Democracy, Governance and Elections) አማካሪዎች አማካኝነት ለምርጫ ቦርድ የበላይ አመራሮች እና ኃላፊዎች ሥልጠና ሰጠ

ሥልጠናው “የምርጫ ተቋማዊ ልህቀት ግንባታ” (Building Institutional Excellence in Elections) በሚል ርዕስ የተሰጠ ሲሆን የቦርድ አባላት፤ የጽ/ቤት ኃላፊዎች፤ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች እና ከቦርዱ የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የተውጣጡ በድምሩ 25 የሚሆኑ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈውበታል፡፡

ሥልጠናው በዋናነት የምርጫ አስተዳደርን፣ መዋቅራዊ አደረጃጀትን፣ ዕቅድን፤ የድርጅት ባህልን፤የውስጥ እና የውጭ ተግባቦትን፤አጋርነትን እና ስኬታማ የአመራር ሂደትን በተመለከቱ ሃሳቦችን ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ዓለም አቀፍ የምርጫ አስተዳደር ክፍሎችን /Election Management Bodies/ የናሙና ጥናቶችን፤ከተግባራዊ ልምምዶች ጋር ያካተተ እና እና በአጠቃላይም በምርጫ አስተዳደር ውስጥ ተቋማዊ ልህቀት (Institutional Excellence) እንዴት መገንባት እንደሚቻል የሚያሳዩ ፅንሰ-ሀሳቦችን እና መርሆችንም ያካተተ ነበር። ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 4 ቀን 2016ዓ.ም. በተካሄደው በዚህ ሥልጠና ሥልጠናቸውን ተከታትለው ላጠናቀቁ ሠልጣኞች BRIDGE (Building Resources in Democracy, Governance and Elections) የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡

Share this post