Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቦርዱ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየሠጠ ይገኛል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቦርዱ የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትል እና ግምገማ የሥራ ክፍል አስተባባሪነት 45 ለሚሆኑ የቦርዱ የክልል ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የዲፓርትመንት ኃላፊዎች እና ኤክስፐርቶች በዕቅድ ዝግጅት (Planning)፣በጀት አያያዝ (Budgeting)፣ ክትትል እና ግምገማ (Monitoring and Evaluation)፣ የአፈጻጸም ሪፖርት አዘገጃጀት (Reporting)፤የሠራተኛ ምዘና (Performance Evaluation and Coach for Performance) ላይ ያተኮረ ሥልጠና እየሠጠ ይገኛል፡፡

ከታህሣሥ 22 እስከ ታህሣሥ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ የሚቆየው ሥልጠና ዋና ዓላማ እያንዳንዱ ኃላፊ የሥራ ክፍሉን ተግባራት ለማቀድ፤በጀት ለመመደብ እና ደረጃውን የጠበቀ ሪፖርት ለማቅረብ የሚያስችለውን ዕዉቀት እና ክህሎት ለማስጨበጥ ያለመ ነው፡፡

በዚሁ ሥልጠና ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳስገነዘቡት ሥልጠናው የቦርዱ የስትራቴጂክ ዕቅድ (Strategic Plan) መዘጋጀቱን ተከትሎ ለሚዘጋጀው የአምስት ዓመት የኦፕሬሽናል ዕቅድ (Operational Plan) ዝግጅት የየሥራ ክፍሎቹ የሚያስፈልጋቸውን ዕዉቀት እና ክህሎት እንዲያዳብሩ እንደሚያስችላቸው ገልፀው የቦርዱን አሠራርም ወደላቀ ደረጃ በማሻገር ረገድም ትልቅ ግብአት እንደሚሆን ያላቸውን ዕምነት ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ታህሣሥ 22 ቀን 2016 ዓ.ም.

Share this post