Skip to main content

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሾሙ

ከዚህ ቀደም ቦርዱን በሰብሳቢነት ሲመሩ የነበሩት ብርቱካን ሚደቅሳ ከነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን መልቀቃቸው ተከትሎ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ አድርጎ ሾሟል፡፡

ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ቀደም ብሎም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጽሕፈት ቤት ኃላፊ በመሆን ከየካቲት 2012 ዓ.ም እስከ የካቲት 2015 ዓ.ም ማገልገላቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከወዲሁ ለወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ታህሣሥ 9 ቀን 2016 ዓ.ም.

Share this post