የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተማሪዎች እና ወጣቶች መካከል በስነዜጋ እና በዲሞክራሲያዊ ምርጫ እሳቤዎች ዙርያ የክርክር መድረኮችን ለማዘጋጀ ፍላጎት ላላቸው ተቋማት ጥሪ ያቀርባል።

በመሆኑም ከዚህ በፊት ጥያቄ/ ማብራሪያ ያስገባችሁም ሆነ በዚሁ ጉዳይ ላይ ፍላጎት ያላችሁ መንግስታዊ ያልሆናችሁ ተቋማት እና ሚዲያዎች በተናጠል ወይም በጋራ የምርጫ ክርክር ዝርዝር የፍላጎት መግለጫ ወረቀት (Expression of interest) ለቦርዱ እንድታቀርቡ ጥሪ ያቀርባል።

ማንኛውም ክርክር ለማከናወን የሚያስብ ተቋም የሚመለከቱትን ዋና ዋና ነገሮችን ያሟላ የፍላጎት መግለጫ ሊያቀርብ ይገባል።

  • ተቋሙ ሊያከናውነው ያቀደው ክርክር ግልጽ ዓላማ፤
  • ተቋሙ ሊያከናውነው ያቀደው ክርክሩ የሚከናወንበት መንገድ (mode of engagement)፤
  • ተቋሙ ያዘጋጀው የክርክር ስነምግባር ደንብ (code of conduct)፤
  • የክርክሩ ቁጥር ብዛት፣ የተሳታፊዎች ሁኔታ፤
  • ክርክሩ የሚካሄድባቸው ቦታዎች፤
  • ለህዝብ የሚቀርብበት ሁኔታ እና የተደራሽነት መጠን፤
  • የአከራካሪ አመራረጥ ሂደት፣ መስፈርት እና መመዘኛ፤
  • ተቋሙ ያዘጋጀው የክርክር በጀት ፤
  • ተቋሙ ለክርክሩ የሚያወጣው የገንዘብ ምንጭ፤
  • ተቋሙ ክርክሩን የሚያከናውንባቸው ቋንቋዎች እና የመሳሰሉት፡፡

ከላይ ከተጠቀሱት ዋና ዋና ጉዳዮች በተጨማሪ ምክረሃሳብ የሚያስገቡ ተቋማት አስፈላጊ ነው የሚሉትን ዝርዝር እቅድ በምክረሃሳባቸው ውስጥ አካተው ማቅረብ ይችላሉ። የፍላጎት መግለጫ ወረቀት እስከ ታህሳስ 10 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በምርጫ ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ቁጥር 106 በግንባር ወይም በ votersedu [at] nebe.org.et ኢሜይል አድራሻ ሊቀርብ ይችላል። ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0995003865 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

 

ማስታወቂያ
ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም