Skip to main content

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለክልል ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥልጠና ተሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀደም ብሎ በሰራው የፍላጎት ዳሰሳ ግኝት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን አራተኛ ዙር ሥልጠና ለምርጫ ቦርዱ የክልል ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሠራተኞች “ምርጫ ነክ አለመግባባቶችን በምርጫ ሕጉ መሠረት በሚፈቱበት ሂደት፤ በአማራጭ የክርክር አፈታት ሂደቶች፤ በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች እና በስርዓተ ጾታ እና አካታችነት” ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለሶስት ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ከኀዳር 26 እስከ ኀዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በቆየው ስልጠና ወደ 33 የሚደርሱ ከምርጫ ቦርድ የክልል ቅርጫፍ ጽ/ቤቶች የተውጣጡ የየቅርንጫፉ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

ሥልጠናው ከምርጫ ቦርድ የሕግ፤ የፖለቲካ ፓርቲ ጉዳዮች እና የስርዓተ ጾታ የሥራ ክፍሎች ባለሙያዎች እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን በምርጫ ቦርድ የሥልጠና ሥራ ክፍል አስተባባሪነት እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

የስልጠናው በተከታታይ መዘጋጀት በየደረጃው ላሉ የምርጫ ቦርዱ አመራሮች እና ባለሙያዎች በምርጫ እና በምርጫ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ ያላቸውን ዕውቀት እንዲያዳብሩ የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ እንደሚሆን ታምኖበታል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post