የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በወላይታ ዞን ሲያከናወን የቆየዉን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ውጤት የማመሳከሩንና የማዳመሩን ሥራ በማጠናቀቅ በዞን ደረጃ ጊዜያዊ ውጤት ይፋ አድርጓል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በ1,812 ምርጫ ጣቢያዎች ላይ ያስፈጸመውንና 849,896 መራጮች ድምፅ የሰጡበትን የወላይታ ዞን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የውጤት ማዳመሩን ሥራ በዞኑ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሲያከናወን መቆየቱ ይታወቃል። በዛሬውም ዕለት ቦርዱ የውጤት የማመሳከሩንና የማዳመሩን ሥራ በማጠናቀቅ በዞን ደረጃ የጊዜያዊ ውጤቱን ይፋ አድርጓል።