የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በወላይታ ዞን ለሚያስፈጽመው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የተለያዩ የቅድመ ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በወላይታ ዞን ለሚያስፈጽመው የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ የተለያዩ የቅድመ ምርጫ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል። ከነዚህም ተግባራት ውስጥ አንዱ ከአዲስ አበባ ተመልምለው ስልጠና የወሰዱ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ሕዝበ ውሣኔው የሚካሄድበት ወላይታ ዞን ውስጥ ወደሚገኙ 1,804 ምርጫ ጣቢያዎች ማጓጓዝ ይጠቀሳል። ይህንንም ተግባር በትላንትናው ዕለት ሰኔ 5 ቀን 2015 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ዙር 2,495 አስፈጻሚዎች መነሻውን ከሚሊንየም አዳራሽ አድርጎ በዞኑ ወደተመደቡበት የምርጫ ጣቢያዎች የማጓጓዝ ሂደት በዛሬው ዕለት ሰኔ 6 ቀን 2015 ዓ.ም. የተጀመረ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት በሶዶ ከተማ ሁሉም ተገኝተው ወደ ማዕከሎቻቸው ተጉዘው ከፊሎቹ ደርሰዋል።