ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነገው’ለት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ. ም. በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው የሕዝበ ውሣኔው በድምፅ መስጫ ቀን አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አሠራጭቶ አጠናቀቀ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በነገው’ለት ጥር 29 ቀን 2015 ዓ. ም. በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው የሕዝበ ውሣኔው በድምፅ መስጫ ቀን አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶችን በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አሠራጭቶ አጠናቀቀ።
ቦርዱ ሥርጭቱን ያከናወነው በ31 ማዕከላት ሥር ባሉ 3,771 ምርጫ ጣቢያዎች ሲሆን፤ ከነዚህም ውስጥ ሁለቱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች በሚገኙባቸው ብርብርና ቁጫ ላይ የተከፈቱ የተፈናቃይ ጣቢያዎች ናቸው። ሥርጭቱ የተከናወነው ከጥር 25 እስከ ጥር 28 ቀን 2015 ዓ.ም. ሲሆን፤ ምርጫ ጣቢያዎቹም በነገው ዕለት ለሚከናወነው የሕዝበ ውሣኔ የድምፅ መስጠት ሂደት በሙሉ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ። ጣቢያዎቹ በነገው ዕለት ሰኞ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ክፍት የሚሆኑ ሲሆን፤ ቦርዱ መራጮች በተጠቀሰው ሰዓት ወደተመዘገቡበት ጣቢያ በመሄድ ድምፃቸውን እንዲሰጡ ያሳውቃል።