የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በተለያዩ ምክንያቶች እንዲደገም ውሣኔ በተላለፈባቸው ምርጫ ክልሎች ላይ በዚህ ዓመት ምርጫውን ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ ይገኛል።

በዚሁ መሠረት በደ/ብ/ብ/ሕ ክልላዊ መንግሥት ሥር በምቃንና ማረቆ ሁለት ምርጫ ክልል፣ በአፋር ክልል ደሉል ምርጫ ክልል እንዲሁም በቤኒሻንጉል ክልል መንጌ ምርጫ ክልል ላይ ለሚያካሂደው የድጋሚ ምርጫ፤ ምርጫውን የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። ስለሆነም በተጠቁሱት አካባቢዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ አመልካቾች ከጥር 19 እስከ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ እንድታመለከቱ ቦርዱ ያሳውቃል።

የምልመላ መሥፈርት፡‐

• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣

• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣

• የመኖሪያ አድራሻ፦ በምርጫ ክልሉ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ ውስጥ የሆነ/ች፣

• የትምህርት ዝግጅት፦12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣

• የሥራ ቦታ፦ በተጠቀሱት የምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌ እና ምርጫ ጣቢያዎች

• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን በድምሩ 250 ብር

• በክልሉን የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆኑ ይመረጣል፤ ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ።

በመሆኑም ከዚህ በላይ የቀረበውን መሥፈርት የምታሟሉ አስፈጻሚዎች እዚህ ላይ በመጫን ከጥር 19 እስከ የካቲት 3 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባሉት 14 ተከታታይ ቀናት እንዲመዘገቡ ቦርዱ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ፡ በእነዚህ ምርጫ ክልሎች የሚካሄደው የድጋሚ ምርጫ በመሆኑ በስድስተኛው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ የተሣተፋችሁ ምርጫ አስፈጻሚዎች ማመልከቻ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

 

ማስታወቂያ
ጥር 19 ቀን 2015 ዓ. ም.