Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የአፋር ህዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ቦረዱ ያሳለፈዉ ዉሳኔ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ የአፋር ህዝብ ፍትሐዊ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም. ያካሄደውን ጠቅላላ ጉባዔ በሚመለከት ፓርቲው ከሪፖርት ጋር አያይዞ ያቀረባቸውን ሠነዶች ከሕጉ፣ ከፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ እና የቦርዱ ታዛቢዎች ካቀረቡት ሪፖርት አንጻር መርምሮ ውሣኔ አሣልፏል።

ቦርዱ ባደረገው ምርመራ ፓርቲው ያካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ በተደረጉ ምርጫዎች ሕጉንና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንቡን አስገዳጅ ድንጋጌዎች የተቃረኑ አፈጻጸሞችን ገምግሟል። በተጨማሪም በተሻሻለው የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ በዐዋጁ መሠረት ተሻሽለው መቅረብ ያለባቸውን አንቀጾች ቦርዱ የለየ ሲሆን፤ በዛም አግባብ ፓርቲው ይህ ውሣኔ ከተገለጸበት ከታኅሣሥ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት በአራት ወራት ጊዜ ውስጥ ማለትም እስከ ሚያዚያ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ በድጋሜ ጠቅላላ ጉባዔውን እንዲያካሂድ፤ ይህም ሲሆን በድጋሜ የሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ሕጉንና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ የተቀመጡትን ድንጋጌዎች በተከተለ መልኩ መሆን እንዳለበት ቦርዱ ለፓርቲው በላከው ደብዳቤ አሳውቋል።

የውሣኔውን ሙሉ ዝርዝር ደብዳቤ እዚህ ላይ ያገኙታል

Share this post