የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው በሶማሌ ክልል (በጅግጅጋ) በሚገኙ ሁለት ምርጫ ክልሎች ለሚከናወነው ጠቅላላ ምርጫ፤ በምርጫ አስፈጻሚነት ለመሥራት ፍላጎት ላላቸው የቀረበ ጥሪ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ ምክንያቶች 6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው የተወሠኑ የምርጫ ክልሎች ላይ በተያዘው ዓመት ምርጫ ለማከናወን የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በማካሄድ ላይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት በሶማሌ ክልል (በጅግጅጋ) ሁለት በአንድ ምርጫ ክልል ለሚያካሂደው የድጋሚ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ሠራተኞችን በጊዚያዊነት ለመቅጠር ይፈልጋል። ስለሆነም በጅግጅጋ ከተማ እና በዙሪያዋ በሚገኙ ወረዳዎች ውስጥ የምትኖሩ በምርጫ አስፈጻሚነት “በገለልተኝነት” ማገልገል የምትፈልጉ እና ከፓርቲ አባልነት ነፃ የሆናችሁ ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንድታመለከቱ ቦርዱ ይጠይቃል።
የምልመላ መሥፈርት፡-
• ዕድሜው/ዋ ከ18 ዓመት በላይ የሆነ/ች፣
• የማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ አባል ያልሆነ/ች፣
• መኖሪያ አድራሻ፦ በጅግጅጋ እና በዙሪያው ወረዳ ውስጥ የሆነ/ች፣
• የትምህርት ዝግጅት፦ ከ12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
• የክፍያ ሁኔታ፡- በቀን ብር 250
• በክልሉ የሥራ ቋንቋዎች መግባባት የሚችል/የምትችል ቢሆን ይመረጣል፤
• የሥራ ቦታ፦ በጅግጅጋ ሁለት ምርጫ ክልል ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች እና ምርጫ ጣቢያዎች
• ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፤ ከዚህ በፊት በምርጫ ክልሉ የተሣተፉ አስፈጻሚዎች በዚህኛው ምርጫ ማመልከት አይችሉም።
በመሆኑም ከዚህ በላይ የቀረቡትን መሥፈርቶች የምታሟሉ አስፈጻሚዎች ጅግጅጋ በሚገኘዉ የቦርዱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በመገኘት ከጥር 8 እስከ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት በመገኘት እንድትመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥር 04 ቀን 2015 ዓ.ም.