የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደ/ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖች እና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ እያከናወነ ባለው የመራጮች ምዝገባ ሂደት፤ በቦርዱ የኦፕሬሽን ሥራ ክፍል በተዋቀሩ የክትትልና የቁጥጥር ቡድን አማካኝነት በዎላይታ እና በጎፋ ዞኖች በሚገኙ የተወሠኑ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ መሠረታዊ የሆኑ የሕግ ጥሠቶች መፈጸማቸውን ማረጋገጡ ይታወሳል። ይህንንም ተከትሎ ቦርዱ ባሳለፈው ውሳኔ ጣቢያዎቹ ላይ የተደረገው ምዝገባ እንዲሠረዝ፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደቱም ሙሉ በሙሉ እንዲቆምና እንዲሁም የጣቢያዎቹ ሠራተኞች ከኃላፊነታቸው እንዲነሡ፣ የመራጮች ምዝገባውም አዲስ ሠራተኞች ተመልምለው በድጋሚ እንዲደረግ መመሪያ በሰጠው መሠረት፤ የመራጮች ምዝገባው በተሠረዘባቸው ጣቢያዎች ከታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ጥር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. የመራጮች ምዝገባ ስለሚካሔድ፤ ቀደም ሲል በእነዚህ ጣቢያዎች የተሠረዙ መዝገቦች ላይ ሕጉን ተከትሎ የተመዘገቡት እንዲሁም አዲስ መመዝገብ የሚፈልጉ መራጮች በተጠቀሱት ቀናት (ከታኅሣሥ 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ውጪ) በጣቢያዎቹ ቀርበው እንዲመዘገቡ ቦርዱ ጥሪውን ያቀርባል።

ቦርዱ በጣቢያዎቹ ላይ ክትትሉን አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ዳግመኛ መሠረታዊ የሕግ ጥሠት የሚፈጸም ከሆነ በአካባቢው የሚካሄደውን የመራጮች ምዝገባ ሙሉ ለሙሉ የሚሠርዝ መሆኑን ያሳውቃል።

የድጋሚ ምዝገባ የሚደረግባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር

  • በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ዱቦ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ዱቦ
  • በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ዶላ ምርጫ ጣቢያ ሦስት ንዑስ ጣቢያ
  • በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ቤታሎ ለ
  • በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ጫማ ሄምቤቾ ምርጫ ጣቢያ አምስት
  • በዎላይታ ዞን በአረካ ማዕከል ወርሙማ ምርጫ ጣቢያ ወርሙማ ሀ
  • በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ማንቴ ጌራራ ምርጫ ጣቢያ ማንቴ ጌራራ ሦስት
  • በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ቶሜ ጌሬራ ምርጫ ጣቢያ ቶሜ ጌሬራ አራት
  • በዎላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ማዕከል ዋጭጋ ቡሻ ምርጫ ጣቢያ ዋጭጋ ቡሻ 02
  • ጎፋ ዞን ሳውላ ማዕከል ጃዉላ ጎሬ አዳ ምርጫ ጣቢያ
  • ጎፋ ዞን ሳውላ ጃዉላ ውጋ መሸተላ ምርጫ ጣቢያ ሀ
  • ጎፋ ዞን ሳውላ ማዕከል፣ ቡልቂ ከተማ ምርጫ ጣቢያ ቡልቂ 01 ሀ
  • ጎፋ ዞን በኡባ ደብረ-ፀሐይ ማዕከል ገልጣ ሜላንቴ ምርጫ ጣቢያ ገልጣ ሀ
  • ጎፋ ዞን በኡባ ደብረ-ፀሐይ ማዕከል በቶ ታዉን ምርጫ ጣቢያ ሁለት
  • ጋሞ ዞን ብርብር በፋርጎሳ ምርጫ ጣቢያ
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ሀ1
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ለ2
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2_3
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2_2
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2-1
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሳ 1ሀ
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ሀ
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 2
  • ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ማዕከል ማዞ ዶይሣ ምርጫ ጣቢያ ማዞ ዶይሣ 1ለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

 

ማስታወቂያ
ታኅሣሥ 24 ቀን 2015 ዓ.ም.