Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የምርጫ ጣቢያዎችን አቋቋመ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ/ክልላዊ መንግሥት ሥር በሚገኙ ስድስት ዞኖች (ኮንሶ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ወላይታ፣ ጋሞ ፣ ጌዴኦ፣ ጎፋ) እና አምስት ልዩ ወረዳዎች (ቡርጂ፣ ባስኬቶ፣ አሌ፣ አማሮ፣ ዲራሼ) ላይ ለሚያካሂደው ሕዝበ ውሣኔ ከታኅሣሥ 11 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የመራጮች ምዝገባ በማከናወን ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቦርዱ ከዚሁ ጎን ለጎን ለመጀመሪያ ጊዜ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በሕዝበ ውሣኔው የሚሣተፉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ሲሠራ የቆየ ሲሆን፤ በአሁኑም ሰዓት በአንድ ዞን እና በሦስት ልዩ ወረዳዎች ላይ በሚገኙ የተፈናቃይ ማቆያ ካምፕ ውስጥ ላሉ መራጮች፤ ሰባት ልዩ ምርጫ ጣቢያዎችን ማለትም በኮንሶ 3፣ በአሌ 3 እና በዲራሼ 1 ምርጫ ጣቢያዎችን በማቋቋም፤ የመራጮች ምዝገባን የተመለከተ “ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች” ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች የተዋረድ ሥልጠና ሰጥቷል፤ ለመራጮች ምዝገባ የሚውሉ ቁሳቁሶች ሥርጭቱንም እንዲሁ አጠናቋል።

በዚህም መሠረት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የመራጮች ምዝገባ ከነገ ቅዳሜ ታኅሣሥ 22 እስከ ታኅሣሥ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚከናወን ይሆናል።

Share this post