Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለማስፈጸም ለተመለመሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ላይ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚያካሂደውን ሕዝበ ውሣኔ ለማስፈጸም ለተመለመሉ የምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች የመራጮች ምዝገባ ማስፈጸም ተግባራትን የተመለከተ ሥልጠና ከታኅሣሥ 4 እስከ 10 ቀን 2015 ዓ.ም ሰጠ።

ሥልጠናው በስድስቱ ዞኖችና አምስቱ ልዩ ወረዳዎች ላይ በሚገኙ 31 ማዕከላት ለሁለት ቀናት በተለያዩ ዙሮች የተሰጠ ሲሆን፤ ሥልጠናውም የመራጮች ምዝገባን ለማካሄድ የሚያስችሏቸውን መሠረታዊ የፅንሰ ሃሳብና የተግባር ልምምድ አካቷል ።

ስለሕዝበ ውሣኔው አደረጃጀት፤ ስለሚኖረው የሥራ ኃላፊነትና ድርሻ፤ የቅድመ ምዝገባ ጊዜ ተግባራት፣ ለመራጮች ምዝገባ ጥቅም ላይ ስለሚውሉ ቁሳቁሶች፣ የመራጮች ምዝገባ ቁሳቁሶች የሚታሸጉበትና የሚጓጓዙበት ሥርዓት፣ የመራጮች ምዝገባ ሂደት፣ የመራጮች መዝገብ ይፋ የሚደረግበት አግባብ፣ እንዲሁም ሥርዓተ-ፆታ እና አካታችነት በሥልጠናው ትኩረት ከተደረገባቸው ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች ውስጥ ይጠቀሳሉ። ሥልጠናውን ወስደው ያጠናቀቁ ምርጫ አስፈጻሚዎች ወደ ተመደቡባቸው ምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ የሕዝበ ውሣኔውን የመራጮች ምዝግባ የሚያከናውኑ ይሆናል::

Share this post