Skip to main content

ማሳሰቢያ: በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ መዘገብ ለምትፈልጉ መገናኛ ብዙኃን አካላት

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደቡብ ብ/ብ/ሕ ክልል በሚገኙ ስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች ማለትም በጋሞ፣ ጎፋ፣ ወላይታ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ጌዲዮ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም ቡርጂ፣ ደራሼ፣ ባስኬቶ፣ አሌ እና አማሮ ልዩ ወረዳዎች ላይ የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔ መዘገብ ለምትፈልጉ የመገናኛ ብዙኃን አካላት ጥቅምት 21 ቀን 2015 ዓ.ም. የምዝገባ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል። በዚህም መሠረት የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫን ለመዘገብ ከቦርዱ የዕውቅና ባጅ ያገኙ የመገናኛ ብዙኃን አካላት፤ ሀገራዊ ምርጫውን ለመዘገብ የተሰጣቸው ባጅ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች ላይ በሚካሄደው ሕዝበ ውሣኔ ጥቅም ላይ መዋል የማይችልና አገልግሎቱ ያበቃ መሆኑን በመገንዘብ እንደገና ማመልከት እንደሚጠበቅባቸው ቦርዱ ያሳውቃል።

ስለሆነም ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. የሚካሄደውን ሕዝበ ውሣኔው መዘገብ ለምትፈልጉ የመገናኛ ብዙኃን አካላት፤ ቦርዱ የአመልካቾችን መረጃ አደራጅቶ ባጆቹን ለማዘጋጀት ያለው ጊዜ አጭር በመሆኑ እስከ ኅዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም. ተከታዩን ማስፈንጠሪያ እዚህ ላይ በመጫን እና አስፈላጊ የሆኑ ሠነዶችን በማሟላት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

በተለያየ ምክንያት ኦን-ላይን ማመልከት ለማትችሉ፤ የማመልከቻ ፎርሙን በመሙላት (በአካል ማመልከት ለሚፈልጉ የማመልከቻ ፎርሙን ተከታዩን ማስፈንጠሪያ በመጫን ማውረድ ይችላሉ። ይህ ሰነድ እና የተጠየቁ ሠነዶችን አባሪ በማድረግ ጥያቄያችሁን ቦሌ ፍላሚንጎ ሬስቶራንት አጠገብ በሚገኘው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋናው መሥሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ. 308 በአካል በመቅረብ ማመልከቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

የሚዲያ ጉዳይን የተመለከተ ጥያቄ ካሎት contact [at] nebe.org.et ወይም በሥራ ሰዓት በስልክ ቁጥር +251905053051 (የሚዲያ ጉዳይ በተመለከተ ብቻ) ሊያገኙን ይችላሉ።

Share this post