Skip to main content

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት መካከል የጋራ ስምምነት ሠነድ (Memorandum of Understanding) ተፈረመ

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እና በጋራ ምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ መብራቱ አለሙ (ዶ/ር) አማካኝነት ዛሬ ጥቅምት 9 ቀን 2015 ዓ.ም. የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሠነድ ምክር ቤቱ መጋቢት 2011 ዓ.ም በፓርቲዎች መካከል የተፈረመውን የቃል ኪዳን ሠነድ ዐላማ ለማሳካት ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ቦርዱ ድጋፍ ለማድረግ ይችል ዘንድ፤ እንዲሁም ምክር ቤቱም የሚሰጠውን ድጋፍ በመግባቢያ ሠነዱ ውስጥ በተጣለበት ኃላፊነት መሠረት ለታለመለት ዐላማ ማዋሉን ለማረጋገጥ የተፈረመ ነው፡፡

በዚህ የመግባቢያ ስምምነት መሠረት ቦርዱ ለምክር ቤቱ ድጋፍ ከሚያደርግባቸውና ከምክር ቤቱ ጋር የጋራ መግባባት ከተደረሰባቸው ውስጥ : -

• የምክር ቤቱ ገጽታ ግንባታ ስራዎች (ለመጽሔት ዝግጅት፤ ለማስታወቂያና ተዛማጅ ስራዎች )

• ፕሬስ ኮንፈረንስ ማዘጋጀት፣

• ለአስተዳደራዊ ወጪዎች፤ ማለትም ለሥራ ፈጻሚዎች የሚውሉ የተለያዩ ወጪዎች ተግባራትን ለማከናወን የሚሆን፤ ም/ቤቱ ወደ ክልል የጋራ ም/ቤቶች ለድጋፍና ክትትል ለሚያደርጋቸዉ እንቅስቃሴዎች የሚደረግ ወጪን መሸፈን ይጠቀሳሉ።

ቦርዱ ቀደም ሲል በሕግ በተሰጠውን ሥልጣንና ኃለፊነት ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎችን የመከታተል እና የመደገፍ ኃላፊነት ያለበት እንደመሆኑ፤ ለእያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ከሚያደርገው ድጋፍ በተጨማሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስብስብ የሆነውን ምክር ቤት በመደገፍ የበለጠ ተደራሽ እና ፓርቲዎች በዴሞክራሲ ግንባታ፣ የሕግ የበላይነት መስፈን እና በሰላም መረጋገጥ ላይ ያላቸውን ሚና የበለጠ ለማጎልበት በማሰብ ለጋራ ምክር ቤቱ ቢሮና አስፈላጊ የቢሮ ቁሳቁሶችን፤ እንዲሁም ለሥራ እንቅስቃሴ የሚረዳ የመኪና ድጋፍ ማድረጉ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

9 ቀን 2015 ዓ.ም.

Share this post