የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ ከተመዘገቡት የመራጮች መዝገብ መረጃ ውስጥ በሙከራ ደረጃ ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ሥራ (pilot Voters List Digitization and Auditing) ለማሠራት ባቀደው መሠረት ሥራውን ለማከናወን የሚችሉ ብቃት ያላቸውን ባለሞያዎች መልምሎ ለአጭር ጊዜ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም መረጃን ወደ መረጃ ቋት የማስገባት (Data Encoding) የሥራ ልምድ ያላቸሁ፡-

1. በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ ቢያንስ በድግሪ የተመረቃችሁ

2. ቢያንስ የአንድ ዓመት የሥራ ልምድ (በተለይ በዳታ ማስገባት (Data encoding) ላይ ልምድ ያላቸው ቢሆን ይመረጣል)

3. የሥራ ቋንቋውን አቀላጥፈው ማንበብና መፃፍ የሚችሉ

4. ሴቶች አመልካቾች የሥራ ልምዱ ካላቸውና ሌሎች መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሆነ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል።

ሥራውን በቅልጥፍና፣ በጥራትና በሥነ ምግባር ማከናወን የምትችሉ አመልካቾች ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ባለው ጊዜ እንድታመለክቱ እየጠየቅን የመጀመሪያውን የምልመላ ደረጃ ያለፉ አመልካቾች በኦንላይንና በአካል ፈተና የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ሊንኩን ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

ማሳሰቢያ፡ የሥራ ቦታው አዲስ አበባ ሲሆን፣ አመልካቾች ሥራው ከሚከናወንባቸው አማርኛ፣ ኦሮሚኛ፣ ሶማሊኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች መካከል በሚገባ መጻፍ ማንበብ እና መረዳት በምትችሉት ቋንቋ እንድታመለከቱ እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

የስራ ማስታወቂያ
ጥቅምት 03 ቀን 2015ዓ.ም.