የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 100 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት መንግስት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የሚሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ ለመወሰን መመሪያ በማውጣትና በስራ ላይ በማዋል ለ2014 በጀት ዓመት የተፈቀደውን ድጋፍ በመስፈርቱ መሠረት አከፋፍሎ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በከፈቱት የተለየ የባንክ ሂሣብ ቁጥር ገቢ ማድረጉ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በ2014 በጀት ዓመት በመስፈርቱ መሠረት በባንክ ሂሣብ ቁጥራችሁ ገቢ የሆነውን የፋይናንስ ድጋፍ በአዋጁ አንቀፅ 82 መሠረት በተመሰከረለት የውጭ ኦዲተር በማስመርመር እስከ ኅዳር 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ለቦርዱ ሪፖርት እንድታቀርቡ ያሳውቃል፡፡
በተጨማሪም የተሰጣችሁ ድጋፍ በከፈታችሁት የተለየ የባንክ ሂሣብ ቁጥር ገቢ ስለመደረጉ የሚያሳይ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ በአስቸኳይ እንድታቀርቡ ቦርዱ ያሳውቃል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የስራ ማስታወቂያ
ጥቅምት 01 ቀን 2015ዓ.ም.