የምርጫ አስፈጻሚዎች ሰርተፍኬት አወሳሰድ ማብራሪያ


ሰርተፍኬቱ ለማን ነው የተዘጋጀው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እና መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ማካሄዱ ይታወቃል። በዚህም ምርጫ ላይ ለተሳተፉት፤

  • ምርጫ ጣቢያ አስፈጻሚዎች
  • አይ ሲ ቲ ባለሞያዎች
  • ዳታ ኢንኮደሮች
  • ምርጫ ክልል አስፈጻሚዎች
  • ዞን ምክትል አስተባባሪዎች እና
  • ዞን አስተባባሪዎች ሰርቲፊኬት ተዘጋጅቷል።

ሰርተፍኬቱ እንዴት መውሰድ ይቻላል

  1. ሰርተፊኬቱን ይህንን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የሚያገኙት ሲሆን ሰርተፊኬቱን ለማግኘት ደሞዝ የተቀበሉበትን የባንክ አካውንት ያስገቡ፤
  2. ወደ ፖርታሉም ከገቡ በኋላ ያስገቡትን መረጃ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠው ሰርተፊኬቱን ማውረድ ይችላሉ፤
  3. ሰርተፊኬቱን ከማውረድዎት በፊት በሰርተፊኬቱ ላይ ያለው መረጃ ትክክለኛ መሆኑን ያረጋግጡ፤
  4. የመረጃ ስህተት ካጋጠሞት ቀጥሎ በሚገኘው ግፅ ላይ ትክክለኛውን መረጃ ያስገቡ፤

ሰርተፍኬትዎ ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ