የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን በአብዛኛው የአገራችን ክፍሎች አከናውኖ ያጠናቀቀ ሲሆን በቢኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ደግሞ በታህሳስ ወር ምርጫውን ለማከናወን የጊዜ ሰሌዳ አውጥቶ ተግባራትን ማከናወን ጀምሮ እንደነበር ይታወቃል።
የኢ.ፌዲ.ሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሚኒስትሮች ምክር ቤት የተዘጋጀውን አገር አቀፍ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትላንትና ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ.ም ማጽደቁን ተቀትሎ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የምርጫ ሰሌዳን እና ዝግጅትን ያቋረጠ ( suspend) መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ጥቅምት 26 ቀን 2014 ዓ.ም