የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አጠቃላይ ምርጫን መዘገብ ለሚፈልጉ ለሀገር ውስጥና ለውጭ የብዙኃን መገናኛ አካላት እና ጋዜጠኞች በተለያየ ጊዜ የፍቃድ ጥያቄያቸውን ለቦርዱ እንዲያቀርቡ ጥሪ በማድረግ መዘገብ የሚያስችላቸውን ልዩ የዘገባ ባጅ መስጠቱ ይታወቃል። ልዩ ባጅ የወሰዱ የሀገር ውስጥ የብዙኃን መገናኛ አካላት እና ጋዜጠኞች ቦርዱ በቀጣይ መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም. ምርጫ ባልተደረገባቸው አካባቢዎችና የድጋሜ ምርጫ እንዲሁም የሕዝበ ውሣኔ የሚያካሂድባቸው አካባቢዎች አስመልክቶ የሚኖረው የምርጫ ሂደትን ለመዘገብ ቀደም ሲል ቦርዱ የሰጣቸውን ባጅ እንደሚጠቀሙ ለማሳወቅ ይወዳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ማስታወቂያ
ጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም