የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የምርጫ ስነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 እና ቦርዱን ባቋቋመው የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1133/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወኪሎች ፍቃድ ለመስጠት እና ለመከታተል የሚያስችለውን መመሪያ አርቅቆ ማጽደቁ ይታወሳል።
በዚህ መሠረት ለሚቀጥለው 10 ቀን የሚከናወነውን የመራጮች ምዝገባ ሂደትን ለመታዘብ የፓርቲ ወኪል ማቅረብ የሚፈልጉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ወኪሎችን በተሰጡት ቅፆች በመጠቀም ይህ ጥሪ ከወጣበት ቀን ጀምሮ
በሶማሌ ክልል ለሚወዳደሩ- በሶማሌ ብሔራዊ ክልል የቦርዱ ጽ/ቤት
በሐረሪ ክልል ለሚወዳደሩ ፓርቲዎች- በቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት
በደ/ብ/ብ/ህ ክልል ለሚወዳደሩ ፓርቲዎች - በቦርዱ ዋና መስሪያ ቤት እውቅና የሚሰጣቸውን ወኪሎች ዝርዝር በማስገባት መውሰድ ይችላሉ። በድምፅ መስጫ ቀን ተጨማሪ ወኪሎች እውቅና የሚሰጥ ሲሆን ይህም በየምርጫ ክልሉ የሚከናወን ይሆናል።
*********************************************************************
የፓርቲ ወኪሎች ፍቃድ መታወቂያ ለማግኘት የሚያስፈልጉ እና ለቦርዱ መቅረብ ያለባቸው ሰነዶች
1. ፓርቲው ወኪሎች ስም ዝርዝር እና በወኪልነት የሚንቀሳቀሱበትን ምርጫ ክልል እንዲሁም የወኪልነት አይነታቸውን የሚያሳይ የተሞላ እና የተፈረመ ቅጽ (ቅጹ ከቦርዱ ጽኅፈት ቤት የሚገኝ)
2. የፓርቲው ህጋዊ ወኪሎች መሆናቸውን እና ህግ አክብረው የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን የሚገልጽ በፓርቲው ሃላፊ የተፈረመ የቃለመሃላ ሰነድ (ሰነዱ ከቦርዱ ጽኅፈት ቤት የሚገኝ)
3. በፓርቲው ሃላፊ የተፈረመ እና በምን ያህል የምርጫ ክልሎች ምን ያህል ወኪሎች መታወቂያ እንደሚያስፈልጋቸው የሚገልጽ የእውቅና መጠየቂያ ደብዳቤ ተጨማሪ መረጃዎች
• በፓርቲ ወኪልነት የሚቀርብ/የምትቀርብ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት/አለባት።
- ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/ች፣
- እድሜ 21 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣
- የመምረጥ እና መመረጥ መብቱ/ቷ በሕግ ያልተገደበ፣
- የታወቀ ብልሹ ስነ-ምግባር የሌለበት/ባት፣
- ማንበብ እና መፃፍ የሚችል/የምትችል እና
- በእጩ ተወዳዳሪነት ያልተመዘገበ/ች መሆን አለበት/ባት፡፡
• አንድ ተወዳዳሪ ፓርቲ የፓርቲ ወኪሎችን ማቅረብ የሚችለው እጩ ባቀረበበት የምርጫ ክልል ብቻ ሲሆን በአንድ ምርጫ ክልል እስከ 7 ተዘዋዋሪ እና 2 ተቀማጭ ወኪሎችን ማቅረብ ይቻላል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ>