የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም በዋናነት ያስፈጸመ ሲሆን በእለቱ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ላልተከናወነባቸው እና የመራጮች ምዝገባ በድጋሚ ለሚከናወንባቸው ቦታዎች ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ከነዚህ ስራዎችም መካከል ምርጫ አስፈጻሚዎችን ሁኔታ እና ቁጥር መገምገም አንደኛው ስራ ነው። ምርጫ አስፈጻሚዎች የምርጫ ሂደቱ ዋና አካል መሆናቸውን በመረዳት እና ስራውም ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቅ በመሆኑ እንዲሁም የምርጫ ሂደቱ ከተጀመረ በኋላ የሰው ሃይል እጥረት እንዳይፈጠር በማሰብ በሶማሌ ክልል፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል እንዲሁም በሐረሪ ክልል ተጨማሪ የሰው ሃይል ምልመላ ማከናወን እንዳለበት አምኗል።

በዚህም መሰረት

በቦርዱ ድረገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚገኘውን ፎርም በመጠቀም ነሃሴ 14፣ 15 እና 16 ቀን 2013 ዓ.ም ብቻ ማመልከት ትችላላችሁ። የስራው ቆይታ ለ 30 ቀናት ሲሆን ክፍያው በቀን አበል የሚታሰብ ነው።

ማመልከት የሚቻለው ኦንላየን ብቻ ሲሆን https://nebe.org.et/pworkers/ በመግባት ማመልከት ይቻላል። ማመልከቻው በቦርዱ ድረ ገጽ ላይም ይገኛል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ማስታወቂያ
ነሐሴ 14 2013