ለክልል ወይም ለከተማ ም/ቤት መቀመጫ አንድ መራጭ መምረጥ የሚችለው የእጩዎች ብዛት እንደየምርጫ ክልሉ ይለያያል ። አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 1 እጩ፣ እንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 3 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ደግሞ ላይ 9 እጩዎች አንዳንድ የምርጫ ክልሎች ላይ 14 እጩዎች ወይም ሌላ ቁጥር ያለው የመቀመጫ ብዛት ሊኖራቸው ይችላል።

ብዛቱ የሚወሰነው የምርጫ ክልሉ በክልል ም/ቤቱ ባለው የመቀመጫ ቁጥር ብዛት ነው ። በመሆኑም አንድ መራጭ በክልል ም/ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ መምረጥ የሚችለው የዕጩዎች ብዛት በክልል ምክር ቤት ድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ ከላይ ተፅፎ ይገኛል። በዚህም መሰረት አስፈጻሚዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ሲሰጡ ለመራጩ በምርጫ ጣቢያ ውስጥ እስከ ስንት እጩ መምረጥ እንደሚችል ያስረዳሉ።

vሆኖም ግን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የድምፅ መስጫ ወረቀት ላይ በሀገር ዐቀፍ ደረጃ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች አንድ ዕጩ ብቻ የሚመረጥ ይሆናል። ስለዚህም ከዚህ ቁጥር ገደብ በላይ ምልክት የተደረገባቸው የድምፅ መስጫ ወረቀቶች ዋጋ አይኖራቸውም።

በመሆኑም ድምፅዎን ሲሰጡ በወይን ጠጁ የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት ወረቀት አንድ በክልል ምክር ቤት አረንጓዴ ወረቀት ደግሞ ወረቀቱ ላይ በተጻፈው እና ምርጫ አስፈጻሚው በሚነግርዎ ቁጥር መሰረት መሆኑን አይርሱ። ከተፈቀደው የእጬ ቁጥር በላይ ምልክት አያድርጉ።

ማስታወቂያ
ሰኔ 12 ቀን 2013 ዓ.ም