Skip to main content

መረጃ ለግል እጩ ተወዳዳሪዎች

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከግል እጩ ተወዳዳሪዎች ጋር በተለያየ ግዜ ባደረገው ምክክር መሰረት ቦርዱ የግል እጩ ተወዳዳሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው አምኖበት ለእያንዳንዳቸው የ50 ሺህ ብር ድጋፍ ለመስጠት ወስኗል፡፡

ስለሆነም በምርጫ ቦርድ በግል እጩ ተወዳዳሪነት እውቅና አግኝታችሁ ለ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ የምትወዳደሩ ሁሉ ሙሉ ስማችሁን አድራሻችሁን (ስልክ ቁጥራችሁን፣ ኢሜል) እንዲሁም የባንክ አካውንታችሁን ለፖለቲካ ፓርቲዎች ስራ ክፍል በአካል ወይም በ politicalparties@nebe.org.et ኢሜል አድራሻ ወይም በስልክ ቁጥሮች +251913551505/ +251929289444 የዋትስ አፕ እና ቴሌግራም አፕሊኬሽኖች ላይ እንድትልኩ እናሳውቃለን፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ሰኔ 09 ቀን 2013 ዓ.ም

Share this post