ስለ ጥሞና ወቅት መረጃዎች
የጥሞና ወቅት በቅድመ የምርጫ ዑደት ውስጥ የሚገኝ ጊዜ ሲሆን በኢትዮጵያ የምርጫ ዑደት መመሪያ መሠረት ምርጫ ከመደረጉ በፊት ያሉትን አራት ቀናት ያካትታል፡፡ በጥሞና ወቅት ታዲያ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት፤ ማለትም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ሊተገብሯቸው የሚገቡ ሀላፊነቶች አሉ፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች
- የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎችና ደጋፊዎቻቸው ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ መሠረት የሚየካሂዱት የምርጫ ውድድር እንቅስቃሴ ድምጽ መስጠት ከመጀመሩ ከአራት ቀን በፊት መጠናቀቅ አለበት፡፡
- የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው አራት ቀን ሲቀረው ማንኛውም አይነት የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡ (በኢንተርኔት፣ በማህበራዊ ሚዲያ፣ በግንባር፣ ቤት ለቤት፣ በአደባባይ ፣ በአዳራሽ ስብሰባ ምንም አይነት ቅስቀሳ ማከናወን በጥብቅ የተከለከለ ነው)
- የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ጉዳዮች ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንዲሁም ቃለ-መጠይቆችን ማድረግ አይፈቀድላቸውም፡፡
- ብሄራዊ የምረጫ ቦርድ የሚያወጣቸውንም መመሪዎች ሊፈጽሙ ይገባል፡፡
ለመገናኛ ብዙሀን ተቋማት
- የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት በጥሞና ወቅት ማንኛውንም ምርጫ ተኮር እንቅስቃሴዎችን ማሰራጨት አይፈቀድላቸውም፡፡ በተጨማሪም የፓለቲካ ፓርቲ እጩዎችን አግኝተው ቃለ መጠይቆችን መስራት አይፈቀድላቸውም፡፡
- የመገናኛ ብዙሀን ተቋማት ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የሚወጡ መረጃዎችን የማስተጋባት ሀላፊነት ሲኖርባቸው ከዚህ ውጪ በመመሪያዎች ላይ ያልተደነገጉ ተግባራትነ እንዲፈጽሙ አይፈቀድላቸውም፡፡