Skip to main content

ለፓለቲካ ፓርቲዎች እና ለግል እጩዎች በሙሉ

የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል። በመሆኑም የድምጽ መስጫ ቀን በምርጫ ጣቢያ በመገኘት የሚታዘቡ የፓርቲ ወኪሎቻችሁን እውቅና ለማሰጠት እና ባጅ ለማግኘት በምትወዳደሩበት ምርጫ ክልል ቢሮ በመሄድ ዝርዝራቸውን እንድታስገቡ እናሳውቃለን። ዝርዝር ማስገቢያው ቅጽ እና ቃለመሃላ ፎርም ከዚህ ማስታወቂያ ስር ተያይዟል።

የእጩ ወኪልነት መስፈርቶች

• በእጩ ወኪልነት የሚቀርብ/የምትቀርብ ማንኛውም ሰው የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለበት/አለባት።

1. ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/ች፣

2. እድሜ 21 ዓመት እና ከዚያ በላይ የሆነ/ች፣

3. የመምረጥ እና መመረጥ መብቱ/ቷ በሕግ ያልተገደበ፣

4. የታወቀ ብልሹ ስነ-ምግባር የሌለበት/ባት፣

5. ማንበብ እና መፃፍ የሚችል/የምትችል እና

6. በእጩ ተወዳዳሪነት ያልተመዘገበ/ች መሆን አለበት/ባት፡፡

• አንድ ተወዳዳሪ ፓርቲ ወይም የግል እጩ ወኪሎችን ማቅረብ የሚችለው እጩ ባቀረበበት የምርጫ ክልል ብቻ ሲሆን በአንድ ምርጫ ክልል እስከ 7 ተዘዋዋሪ የምርጫ ክልል ወኪሎች እና በምርጫ ክልሉ ስር ለሚገኙት እያንዳንዱ ምርጫ ጣቢያዎች 2 ተቀማጭ ወኪሎችን ማቅረብ ይችላል።

ለተጨማሪ መረጃ ከቦርዱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የስራ ክፍል መጠየቅ ይቻላል።

ፎርሙን ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post