Skip to main content

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ አጭር መረጃ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምርጫ አስፈጻሚዎችን በመቅጠር የምርጫ ስራን እያስፈጸመ እንደሆነ ይታወቃል። በዚህ ሂደት ውስጥ ካጋጠሙት ችግሮች መካከል አንዱ የሆነው የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ መዘግየት ነው። በተለያየ ወቅት የተለያዩ ክፍያዎች ሲደረጉ ቢቆዩም ከአስፈጻሚዎች ቅሬታ ሲያስነሳ የነበረ ጉዳይ መሆኑ አልቀረም።
የክፍያዎቹ መዘግየት ችግር የነበረው ስልጠና ከወሰዱ አስፈጻሚዎች መካከል ስራ ያልጀመሩ በመኖራቸው እንዲሁም ስልጠና ሳይወስዱ ስራ ላይ የተሰማሩ በመገኘታቸው ትክክለኛው ሂደት ተከትለው ወደስራ የተሰማሩ አስፈጻሚዎችን መለየት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው። እነዚህን ልዩነቶች የታዮባቸው ቦታዎችን ለመለየት እና የኮንትራት ማጣራት ማድረግ ጊዜ ፈጅቷል። በዚህ ሳምንት ብቻ ይህንን ችግር ለመፍታት በተደረገው ጥረት ለ 67,405 የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ ለመፈጸም ተችሏል።
በክልል/ከተማ መስተዳድር ደረጃ ሲታይም
1. ኦሮሚያ - 15,758
2. አማራ -28,950
3. ሲዳማ - 6,257
4. አዲስ አበባ - 4,890
5. ድሬዳዋ - 792
6. ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች - 15,326
7. ጋምቤላ- 1,114
አስፈጻሚዎች ክፍያ የተፈጸመላቸው ሲሆን በቀሩት ክልሎች እና በከፊል ክፍያ የተፈጸመባቸው ቦታዎች የሚገኙ አስፈጻሚዎችን ክፍያ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት እንደምናጠናቅቅ እየገለጽን በሂደቱ ለተፈጠረው መጉላላት አስፈጻሚዎቻችንን ይቅርታ እንጠይቃለን።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post