Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የክልል መስተዳድሮች ማድረግ ስለሚገባቸዉ ትብብር በሚመለከት የፃፈዉ ደብዳቤ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ለሚከናወነው የድምጽ መስጫ ቀን ዝግጅቶቹን እያጠናቀቀ ይገኛል። በመራጮች ምዝገባ ወቅት ካጋጠሙት የትራንስፓርት እና የሎጄስቲክስ ችግሮች ትምህርት በመውሰድ ከክልል መንግስታት ጋር በመነጋገር ለድምጽ መስጫ ቀን የሚያስፈልጉትን እገዛዎች እያስተባበረ ነው።

በዚህም መሰረት ቦርዱ ለክልል መስተዳድሮች ድምጽ መስጫ ቀን ሊያቀርቡት የሚገባውን የትራንስፓርት ትብብር ግዴታ በዝርዝር በጽኁፍ ያሳወቀ ሲሆን ይህም የድምጽ መስጫው ቀን በታቀደለት ሁኔታ እንዲፈጸም ወሳኝ ተግባር ነው። በየክልሎቹ የሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር፣ አስፈላጊውን የመጓጓዥ ብዛት እና ቀኖች ትብብር ከስር በተያያዙት ደብዳቤዎች ላይ ይገኛል።

ደብዳቤዉን ለማግኘት እዚህ ላይ ይጫኑ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post