የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባን ሂደትን አስመልክቶ በተለያየ ወቅት የተለያዩ መረጃዎችን ሲያደርስ እንደነበር ይታወቃል። በተጨማሪም የእጩዎች ምዝገባን አስመልክቶ ሶስት የተለያዩ ምክክሮችን ከፓርቲዎች ጋር አከናውኗል::

በመሆኑም በመጀመሪያ ዙር እጩዎች ምዝገባ የተጀመረባቸው ክልልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ማለትም

- በአዲስ አበባ

- በድሬዳዋ

- በኦሮሚያ

- በሃረሪ

- በጋምቤላ

- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ

የእጩዎች ምዝገባ በትላንትናው እለት ተጠናቋል።

የእጩዎች ምዝገባን ዘግይተው በጀመሩ ክልልሎች እና ቦታዎች ማለትም

- በአማራ

- በሶማሌ

- በአፋር

- በምእራብ፣ምስራቅ ወለጋ ዞን ኦሮሚያ፣ቄለም ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ

- በደ///

- በሲዳማ

በመርሃ ግብሩ መሰረት ዛሬ የካቲት 26 ቀን 2013 . ሊጠናቀቅ እንደሚገባው ይታወቃል።

ነገር ግን በቢሮዎች መከፈት መዘግየት የተነሳ፣ እንዲሁም የትራንስፓርት እና ሌሎች እክሎችን እና የፓርቲዎች አቤቱታዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁለተኛ ዙር የእጩዎች ምዝገባ እስከ የካቲት 30 ቀን 2013 . ድረስ መራዘሙን እያሳወቅን ፓርቲዎች በተሰጡት ተጨማሪ ቀናት ውስጥ ምዝገባቸውን አንዲያጠናቅቁ እናሳስባለን