ለፓለቲካ ፓርቲዎች በሙሉ
1. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎች የመራጮች ምዝገባ እና ተያያዥ ሂደቶችን ለመከታተል ይቻል ዘንድ የፓርቲ ወኪሎችን እውቅና ለመስጠት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። በዚህም መሰረት ቦርዱ ባዘጋጀው ፎርም መሰረት የወኪሎቻችሁን ዝርዝር እና ቃለመሃላ እንድታቀርቡ ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል። ነገር ግን እስካሁን የፓርቲ ወኪሎችን ዝርዝር ያስገባው ፓርቲ አንድ ብቻ በመሆኑ ፓርቲዎች የወኪሎቻቸውን ዝርዝር እና የሚወዳደሩበት (ወኪል የሚሆኑበት) ምርጫ ክልል የሚጠይወቅን ፎርም እና ቃለመሃላ አሟልተው እንዲያቀርቡ ያሳስባል። (የፎርሞቹ ሊንክ ከስር ተያይዟል)
2. የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለፓርቲዎች የሚሰጠውን የመንግስት የበጀት ድጋፍ መስጠት እንደጀመረ ይታወቃል፣ በዚህም መሰረት ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ፓርቲዎች እኩል የሚከፋፈለውን 24 ሚልዮን 656 ሺኅ 50 ብር እያከፋፈከ እንዳለ ይታወቃል። በመሆኑም እስካሁን ለ32 ፓርቲዎች ለእያንዳንዳቸው 483 ሺህ452 ብር ያከፋፈለ ሲሆን ቀሪ ፎርም ሞልታችሁ የድጋፍ ገንዘቡን ያልወሰዳችሁ ፓርቲዎች እንድትወስዱ ያሳስባል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም