ለ6ተኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ እንደሆነ ይታወቃል፣ በአዋጅ ቁጥር 1162/2011 በተደነገገው መሰረት የመራጮች ምዝገባ በብሔራዊ በአላት ቀናት አይከናወንም። በመሆኑም ነገ ሚያዝያ 22 ቀን 2013 ዓ.ም የስቅለት በአል በመሆኑ፣ ሚያዝያ 23 ቀን 2013 ዓ.ም የሰራተኞች ቀን በመሆኑ እና ሚያዝያ 24 ቀን 2013 ዓ.ም የፋሲካ በአል በመሆኑ ምርጫ ጣቢያዎች ዝግ ሆነው እነደሚውሉ ለማሳወቅ እንወዳለን። ሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ሰኞ ሚያዝያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም የሚከፈቱ ይሆናል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
 
ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም