የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው አጠቃላይ ምርጫን ለማስፈጸም 130 ሺህ በላይ አስፈጻሚዎችን መልምሎ የመራጮች ምዝገባን እንዳጠናቀቀ ይታወቃል። በሰኔ 14 ቀን 2013 ለሚካሄደው የድምጽ መስጫ ቀን ተጨማሪ የምርጫ አስፈጻሚዎችን መመልመል ይፈልጋል በመሆኑም

በዚህም መሰረት

  • ለምርጫ አስፈጻሚነት በገለልተኝነት አገራችሁን ለማገልገል የምትፈልጉ
  • ምንም አይነት ፓርቲ አባልነት፣ የዝቅተኛ የአስተዳደር እርከኖች ላይ ሰርታችሁ የማታውቁ
  • ከሲዳማ ህዝበ ውሳኔ ውጪ በሌሎች የቀድሞ ምርጫ የማስፈጻም ተግባራት ላይ ተሳትፋችሁ የማታውቁ
  • የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም ተመጣጣኝ ረጅም አመት የስራ ልምድ ያላችሁ
  • በአጭር ጊዜ ኮንትራንት ለመስራት ፍቃደኛ የሆናችሁ

በቦርዱ ድረገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚገኘውን ፎርም በመጠቀም በሚቀጥሉት አራት ቀናት እስከ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማመልከት ትችላላችሁ። ማመልከት የሚቻለው ኦንላየን ብቻ ሲሆን የማመልከቻ ሊንኩም የሚከተለው ነው።

የመመዝገቢያ ፎርም ለማግኘት     እዚህ ላይ ይጫኑ

ffff

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም