የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለድምጽ መስጫ ቀን አስፈጻሚነት ተጨማሪ አስፈጻሚዎችን እየመለመለ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ተጨማሪ የአስፈጻሚዎች ምልመላ በስራ ላይ ያላችሁ አስፈጻሚዎችን የማይጨምር ሲሆን አሁን ይፋ በሆነው ማመልከቻ ማመልከት አይጠበቅባችሁም።

በመሆኑም የአስፈጻሚዎች ማመልከቻ የወጣው አዲስ በአስፈጻሚነት ለመስራት ለሚፈልጉ እንጂ ከቦርዱ ጋር እየሰራችሁ ያላችሁትን የሚመለከት አለመሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 13 ቀን 2013 ዓ.ም