የመራጮች ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉት10 ቀናት የመራጮች መዝገብ ይፋ ተደርጎ ፓርቲዎች፣ ታዛቢዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ሲመለከቱት የቆዩ ሲሆን የመራጮች መዝገብ ይፋ ማድረግ ሂደት በዛሬው እለት ተጠናቋል። ቦርዱ የመራጮች መዝገብ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ የመጡ አቤቱታዎችን ከፓርቲዎች በመተባበር ለመመርመር እና ለመፍታት ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል። አሁን ግን የመራጮች ምዝገብ ይፋ ማድረጊያ ጊዜ በመጠናቀቁ ፓርቲዎች በሂደቱ የታዘባችሁትን እና መፈታት አለበት የምትሉትን አቤቱታ የምርጫ ክልል እና ጣቢያን በማካተት እስከ ነገ ማታ 11፡30 ድረስ ለቦርዱ እንድታስገቡ እየጠየቅን ቦርዱ የቀረቡለት አቤቱታዎችን ለመመርመር እና ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት የሚያደርግ መሆኑን እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ.ም