Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከአለም አቀፍ ሪፕብሊካን ኢንስቲቲዩት (IRI) ለአለም አቀፍ የዴሞክራቲክ ኢንስቲቲዮት (NDI) የምርጫ ታዛቢ ቡድን የምርጫ መታዘብ እውቅና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከመንግስት ግብዣ መሰረት 6ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ በጋራ ለመታዘብ በጋራ ለሚሰሩት ለአለም አቀፍ ሪፕብሊካን ኢንስቲቲዩት (IRI) ለአለም አቀፍ ዴሞክራቲክ ኢንስቲቲዮት (NDI) የምርጫ መታዘብ እውቅናን ሰጥቷል። ቦርዱ የድርጅቶቹ የጋራ የታዛቢ ቡድን ያቀረበውን የጥናት ዘዴ በማየት እንዲሁም በአለም አቀፍ ታዛቢዎች መሰረታዊ መርህዎችን እና የታዛቢዎች አለም አቀፍ የስነምግባር ደንብ በተከተለ መልኩ እንደሚሰሩ ስምምነት ላይ በመድረስ የመታዘብ እውቅናውን የሰጠ ሲሆን በአለም አቀፉ የኮቪድ ወረርሽኝ የተነሳ የታዛቢ ቡድኑ የሚያከናውነው የመታዘብ ተግባር የስፋት ውስንነት እንደሚኖረውና ይህንንም በሚያደርጋቸው ስራዎች እና ማጠቃለያዎች ላይ የሚገለጽ መሆኑን ታዛቢ ቡድኑ እና ቦርዱ በጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።

ቦርዱ ከዚህ በፊት ለ45 የአገር ውስጥ የምርጫ ታዛቢዎች እውቅና መስጠቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 19 ቀን 2013 ዓ.ም

Share this post