የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ እየተከናወነ እንደሆነ ይታወቃል። በዚህም መሰረት እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ያስገቡ ሲሆን የሚከተሉት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ ተደርጎላቸዋል።

1. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

2. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

3. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

4. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ

5. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ

በተጨማሪ

6. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር - ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል።)

በዚህ መሰረት የምርጫ ምልክቶቻችሁን ያላስገባችሁ የቀነ ገደቡ ማጠናቀቂያ ዛሬ በመሆኑ እንድታስገቡ እያሳሰብን፣ እንድትቀይሩ የተገለፀላችሁ ፓርቲዎች ደግሞ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንድታጠናቅቁ እናሳስባለን። የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎችን ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ቦርዱ ለመግለጽ ይወዳል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ጥር 18 ቀን 2013 ዓ.ም