መልስ - የጊዜ ሰሌዳው ከመውጣቱ አስቀድሞ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተከታታይ ምክክሮች ማድረጉ ይታወሳል፣ በዚህም መሰረት የተነሱት ዋና ዋና ጉዳዮች ሁለት ሲሆኑ አንደኛው ፓርቲዎች እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ አለብን የሚሉት ችግሮች ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ናቸው። ያንን መሰረት አድርጎ የጊዜ ሰሌዳ ከመውጣቱ አስቀድሞ ቦርዱ ሁለት ዋና ዋና ተግባራትን አከናውኗል። አንደኛው በመንግስት በኩል የምርጫ ጸጥታ እቅድ ዝግጅት እንዲኖር እና ቦርዱ ምርጫን የተመለከቱ እቅዱ ቴክኒካዊ መረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ያካተተ እንዲሆን በሂደቱ በመሳተፍ ማረጋገጥ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በየክልሉ ያሉ በፓርቲዎች የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት የሶስትዮሽ መድረክ ማዘጋጀት ነው፣ በዚህም መሰረት በየክልሎቹ ፓርቲዎች የሚያጋጥማቸውን ችግር ለመፍታት የሶስትዮሽ ውይይቶች መከናወን ጀምረዋል።እነዚህ ውይይቶች እስከአሁን ሶስት ክልሎች ላይ የተደረጉ ሲሆን በዚህ ውይይትም ገዥው ፓርቲ፣ በክልሎቹ የሚንቀሳሰቀሱ ፓርቲዎች እንዲሁም ቦርዱ ተገኝተው ዝርዝር አቤቱታዎች ላይ ውይይት በማድረግ መፍትሄዎች ላይ መስማማት ላይ እንዲደርሱ ጥረት እየተደረገ ነው። እነዚህ አሰራሮች ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ይረዳሉ ብሎ ቦርዱ ያምናል።

5