Skip to main content

ሚዲያዎች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ዝግጅትን ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጎብኝተዋል

ሚዲያዎች የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ዝግጅትን ዛሬ መስከረም 22 ቀን 2013 ዓ.ም ጎብኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባዘጋጀው የሚዲያዎች ጉብኝት የምርጫ ኦፕሬሽን በቀድሞ ምርጫዎች እንዴት እንደነበረ እና አሁን የሚኖረው ሂደት ምን እንደሚመስል ገለፃ ተደርጓል።

ሁለት የማሳያ ምርጫ ጣቢያዎችን (Sample polling stations) በመገንባት ቀጣዩ ምርጫ ከቀድሞ የሚለይበት የምርጫ ሂደት በማሳያ ቀርቧል። በመጀመሪያው ማሳያ የቀድሞ ምርጫ ሂደትና ልምዶች፣ በሁለተኛው ማሳያ በቀጣዮ ምርጫ አንድ የምርጫ ጣቢያ ምን እንደሚመስል እና ዋና ዋና ለውጦቹ ለእይታ ቀርበዋል። የሚዲያ ባለሞያዎቹ በቦሌ ካርጎ መጋዘን የሚገኘውንም የቁሳቁስ እሸጋ፣ እንዲሁም በምርጫ ክልል ደረጃ አገልግሎት ላይ የሚውሉ ጄኔሬተሮችን እና ላፕቶፓችንም ጎብኝተዋል።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለመጪው ምርጫ ዝግጅት ከድምፅ መስጫ ወረቀቶች ውጪ የቀሩ ግዢዎችን ማጠናቀቁን በተለያየ ጊዜ ማሳወቁ ይታወሳል። 

Share this post