መልስ - የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው ዋና አላማ ምርጫውን ቀድሞ ባቀደው ቀን ማለትም ነሐሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ማከናወን እንደማይችል ማሳወቅ ሲሆን፣ እዚህ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ጥናት አካሂዷል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተጠሪነቱ ለተወካዮች ምክር ቤት ስለሆነ ውሳኔውንም ለተወካዮች ምክር ቤት አሳውቋል፡፡ ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ምክንያት ምርጫውን ማከናወን ካለመቻሉ በስተቀር የተራዘመ ቀን ቆርጦ አላቀረበም፡፡ ቦርዱ ማድረግ የሚችለው አለመቻሉን ብቻ ገልጾ ሪፓርት ለሚያደርግለት ለተወካዮች ምክር ቤት ማሳወቅ ብቻ ነው፡፡ 
በመግለጫው ተገለጹት የቦርዱ ዋና ዋና ውሳኔዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 
• በኮቪድ19 የተነሳ ቦርዱ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫውን ማካሄድ የማይቻለው መሆኑን በመረዳት ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ በመሰረዝ በሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ለጊዜው እንዲቆሙ ፤
• ቦርዱ የወረርሽኙ ሥጋት ተወግዶ ሁኔታዎች ሲመቻቹ እንደገና ግምገማ በማድረግ አዲስ የምርጫ ኦፕሬሽን እቅድና ሰሌዳ በማውጣት እንቅስቀሴውን እንደሚያስጀምር፤
• በኮቪድ 19 የማይስተጓጎሉ፣ የቦርዱን የምርጫ አፈጻጸም ዝግጁነት የሚጨምሩ፣ሁኔታው ተቀይሮ ተቋሙ ወደ መደበኛ ተግባሩ ሲመለስ በተገቢው ሁኔታ ምርጫን ለማስፈጸም የሚያሥችል ሁኔታን የሚፈጥሩ ተግባራትን እያከናወነ መቆየት እንዳለበት፤ 
• በህገ መንግስቱ በተቀመጠው መሰረት በስራ ላይ የሚገኘው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስልጣን ጊዜው ከሚያበቃበት አንድ ወር አስቀድሞ ቦርዱ አጠቃላይ ምርጫውን ማድረግ የማይችል መሆኑን ም/ቤቱ ተገንዝቦ፣ ከዚህ አንጻር የሚሰጠው ውሳኔ ቢኖር ለመነሻነት ያገለግለው ዘንድ ይህ ውሳኔ እንዲሁም ቦርዱ ያደረገው የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ለህዝብ ተወካዮች እንዲተላለፍለት

1