የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአገራችን በገባው ኮቪድ19 ወረርሽኝን ተከትሎ የተለያዩ የአሰራር መንገዶችን በመቀየስ ስራውን ለማከናወን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህ የአሰራር ለውጥ የተነሳ እንዲሁም ለሁሉም አካላት ደህንነት ሲባል የተለያዩ ጉዳዮች ያላቸው የፓለቲካ ፓርቲዎችን ጠርቶ ማነጋገርን፣ ውይይት ማድረግንም ሆነ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠትን አዳጋች አድርጎታል፡፡ 

ከዚህ በፊት ቦርዱ ኢሜል በመላክ እንደገለጸው ከቦርዱ ጋር የሚደረጉ ግንኙነቶችን እና ውይይቶችን ለማሳለጥ ይረዳ ዘንድ የሚከተሉትን መረጃዎች አሟልታችሁ በሚከተለው የኢሜይል አድራሻ nebepoliticalparties [at] gmail.com እንድትልኩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
• የፓለቲካ ፓርቲው የቢሮ ስልክ 
• የፓለቲካ ፓርቲው ኢሜል አድራሻ
• የፓለቲካ ፓርቲው የተረጋገጠ የማህበራዊ ገጽ ስም እና ሊንክ
• የፓርቲው ሀላፊ የሞባይል ስልክ፣ የዋትስአፕ ቁጥር፣ የቫይበር ቁጥር 
• የሀላፊው ወይም የፓርቲው የስካይፕ አድራሻ 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

            

የጥሪ ማስታወቂያ
መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም.