Skip to main content

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለሚዲያዎች በሙሉ

ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም.

የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔን ለመዘገብ የተዘጋጃችሁ እና የዘገባ ፍቃድ ለማግኘት የጠየቃችሁ የሚዲያ አካላት መታወቂያችሁን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት እና ሀዋሳ የሚገኙ ሚዲያዎች ደግሞ ሀዋሳ ከሚገኘው የቦርዱ ጊዜያዊ ማስተባበሪያ መውሰድ እንደምትችሉ እንገልጻለን። ከቦርዱ ለሚዲያ የተዘጋጀውን መታወቂያ ሳይዙ የምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ መገኘት የምርጫ እና የፓለቲካ ፓርቲዎችን ህግ ጥሰት ሲሆን የምርጫ ጣቢያዎችን በማወክ በህግ የሚያስጠይቅ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

Share this post