Skip to main content

የተዛባ መረጃ ማስተካከያ

ኅዳር 8 ቀን 2012 ዓ.ም.   

ዋልታ ኢንፎርሜሽን ዛሬ ጠዋት በሠራው ዘገባ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ የከተማው ነዋሪ 90 በመቶ ሻፌታን መምረጡ ተረጋገጠ በሚል የሠራው ዘገባ የተሳሳተ መረጃ ሲሆን ምክትል ከንቲባው የመራጮችን ተሳትፎንና ጸጥታን እንጂ የሕዝበ ውሳኔውን ውጤት የሚመለከት ምንም ዓይነት መግለጫ አልሰጡም። የምርጫ ውጤትን ማሳወቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኃላፊነት ብቻ መሆኑ እየታወቀ የሚዲያ አካላት የምርጫን ዓይነት ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ዜናዎች ሲሠሩ ከፍተኛ ጥንቃቄ እና ትኩረት እንዲያደርጉ እንዲህ ዓይነት የተሳሳቱ መረጃዎች ሰላምንና ደህንነት የሚያናጉ በመሆናቸው እና በወንጀልም ስለሚያስጠይቁ ጋዜጠኞች ከዚህ ዓይነት ተግባራት እንዲቆጠቡ ቦርዱ ያሳስባል። 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 

Share this post