የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ የክልልነት የመደራጀት ጥያቄ የህዝበ ውሳኔ አማራጮች አስተያየትና አመለካከቶች ከህዝብ የሚቀርብበት መድረክ ማመቻቸት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ፕሮግራም ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ የሲቪክ ማህራትና በሲዳማ ዞን የምትንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ፍላሚንጎ ፊትለፊት የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ጽህፈት ቤት ወይም በሃዋሳ ከተማ በሚገኘው የቦርዱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ድረስ በመቅረብ እንድትመዘገቡ ቦርዱ ያሳውቃል፡፡

የሲቪል ማህበራት ወኪሎች ለምዝገባ በምትቀርቡበት ወቅት የምትሰሩበትን ዘርፍ የሚያሳይ፣ ስልጣን ከተሰጠው አካል የተሰጣችሁን የማህበራት ምዝገባ ሰነድ ይዛችሁ መቅረብ እንደሚገባችሁ በዚህ አጋጣሚ በአክብሮት ይገልጻል፡፡

ከበጎ ምኞት ጋር
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ማስታወሻ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የላይ የተቀመጠውን ማስታወቂያ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ለሶስት ተከታታይ ቀናት ያስነገረ ሲሆን ለመስማት እድሉ ያልገጠማቸውን ለመድረስ ሲባል በድጋሚ እዚህ አጋርቶታል፡፡
 

የጥሪ ማስታወቂያ
መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም.