የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ9ኙ ክልሎችና ለ2ቱ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ሃላፊነት አወዳድሮ ለመመደብ የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን ለሃረሪ ክልል፣ ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ ለጋምቤላ ክልል፣ ለአማራ ክልል በቂ አመልካች ባለመገኘቱ ከስር የተጠቀሰውን ዝርዝር መስፈርት የምታሟሉ እና በሶስቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር መስራት ለምትፈልጉ የማመልከቻ ጊዜው ከዛሬ ከመስከረም 26 2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ስለተራዘመ ማመልከቻችሁን ማስገባት እንደምትችሉ ያሳውቃል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዋና መስሪያ ቤት ደረጃ የጀመረውን ውስጣዊ አደረጃጀት ሪፎርም በክልል ደረጃ በማስፋት በ9 ክልሎች የሚገኙት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶቹን እንደአዲስ እያደራጀ ይገኛል፡፡ የዚህ ስራ ዋናው አካል የክልል የምርጫ ሃላፊዎችን እንደስራ አመራር ቦርዱ አባላት አመራረጥ ሁሉ የሚመለከታቸው አካላት የተሳተፉበት እንዲሆን ማድረግ ነው፡፡ በዚህም መሰረት ከላይ ለተጠቀሱት ሶስት ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በእጩነት ለመወዳደር የሚፈልጉና ከስር የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ግለሰቦች ማመልከት ይችላሉ፡፡ በዚህም መሰረት በክልል የምርጫ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊነት በዕጩነት የሚቀርቡ አመልካቾች ማሟላት የሚኖርባቸው መስፈርቶች፡-
1. ኢትዮጵያዊ ዜጋ የሆነ/የሆነች፣
2. መደበኛ አድራሻው በምርጫ ክልል ውስጥ ሆኖ የፌዴራሉን መንግስት የሚወዳደርበትን ክልል የሥራ ቋንቋ የመናገርና የመፃፍ ክህሎት ያለው/ያላት፤
3. በአካባቢው ነዋሪ ሕዝብ አመኔታ ያተረፈ/ያተረፈች እና መልካም ሥነ ምግባር ያለው/ያላት፤
4. የማንኛውም ፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች
5. በትምህርት ዝግጅት በተለይ በሕግ፣ በፖለቲካ ሳይንስ፣ በህዝብ አስተዳደር፣ በስታቲስቲክስ፣ በማኔጅመንት፣ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ከምርጫ ጉዳዮች ጋር ተዛማጅነት ባላቸው የትምህርት ዘርፎች ቢያንስ በአንዱ የመጀመሪያ ዲግሪ ያለው/ያላት፤
6. አመልካች የማስተርስ ዲግሪ ያላት/ያለው ከሆነ የአራት ዓመት የሥራ ልምድ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላት/ያለው ከሆነ ደግሞ የአምስት ዓመት የሥራ ልምድ
7. የምርጫ ህጉን፣ ደንብና መመሪያዎችን አንብቦ/አንብባ በመረዳት መተግበር የምትችል/የሚችል
8. በተቋም ነጻነትና እና በገለልተኛነት መርህ መሰረት ለማገልገል ዝግጁ እና ሙሉ ፍቃደኛ የሆነች/የሆነ
አመልካች እጩዎች ለስራው ያላቸውን መነሳሳት የሚገልጽ አንድ ገጽ ማመልከቻ፣ የተሟላ ካሪኩለም ቪቴ፣ የትምህርት ማስረጃ እንዲሁም ሁለት ስለአመልካቹ ብቃት የሚገልጹ ለአመልካቹ ቅርብ ከሆኑ ሰዎች የተጻፉ የድጋፍ ደብዳቤዎችን ከነሃሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሚቀጥሉት 10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የተሟላ ማመልከቻቸውን በኢሜል- electionsethiopia [at] gmail.com፣ በአካል ፍላሚንጎ አካባቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ፤ በፈጣን መልዕክት /EMS/ ወይም በፖስታ ሳጥን ቁጥር 40812 መላክ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ