Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች ለቀረቡለት አቤቱታዎች ምላሽ ሰጠ

የካቲት 26 ቀን 2012 ዓ.ም.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ፓለቲካ ፓርቲዎች ከመመዝገብ በተጨማሪ የተለያዩ ድጋፎችን እንደሚያደርግ ይታወቃል። በዚህም መሠረት ሰሞኑን ከተለያዩ ፓርቲዎች የቀረበለትን አቤቱታ አስመልክቶ ምላሾችን ሰጥቷል። በዚህም መሠረት፣ አቤቱታ ያቀረቡ ፓርቲዎች እና ያቀረቧቸው አቤቱታዎች፦

1. ትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ /ትዴፓ/ - እስር፣ ማስፈራራትና ቢሮ መዘጋት፣

2. ኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ /ኢዜማ / - ስብሰባዎች መሰናከል፣ በጎንደር በደብረብርሃን እና የጸጥታ ኃይሎች ለመሰናከሉ ትብብር ማድረጋቸው፣

3. ኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ /ኦብፓ / - እስር፣ ቢሮ መዘጋት፣ ታፔላ መነቀልና አባላት ማስፈራራት፣

4. ኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ /ኦፌኮ / - የአባላት እስርና ማስፈራራት፣

5. ኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ / - የመስራቾች ፊርማ መነጠቅ እና በተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች የአባላት እስር፣

6. ጌዲዮ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ጌህዴድ/ - ሰነድ መነጠቅና የማሟያ ፊርማ ማሰባሰብ ሂደት መደናቀፍ፣

ሲሆኑ ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን አቤቱታ በማያያዝ የሚመለከታቸውን የመንግሥት አካላት ጉዳዩን ከሚያስረዱ ሰነዶች ጋር የካቲት 26 እና 27 ቀን 2012 ዓ.ም. በቦርዱ ጽህፈት ቤት ቀርበው እንዲያስረዱ ደብዳቤ ልኳል። በዚህም መሠረት ለአቤቱታዎቹ ምላሽ እንዲሰጡ ጥሪ የደረሳቸው ተቋማት የሚከተሉት ናቸው፦

• ትግራይ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳደር፣

• ኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት መስተዳደር፣

• አማራ ፖሊስ ኮሚሽን፣

• ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ፖሊስ ኮሚሽን፣

• ኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን፣

• ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ዝዋይ ባቱ ፖሊስ፣

Share this post