Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ጋር ምክክር አካሄደ

የካቲት 19 ቀን 2012 ዓ.ም.                                                                                                          

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አካል ጉዳተኞች በምርጫ ሂደት ስላላቸው ተሳትፎ እንዲሁም ስለ አዲሱ የምርጫ ህግ አካታችነት ከቦርዱ አመራሮችና ሠራተኞች፣ ከክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተወጣጡ ሠራተኞች፣ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን (ኢአጉብማፌ) እንዲሁም ከተለያዩ የአካል ጉዳተኞች ማህበራት ተወካዮች ጋር ምክክር እያካሄደ ይገኛል።
በምክክሩ ከተነሱት ዋና ዋና ሀሳቦች መካከል፦

• የምርጫ ሂደት ቅድመ ምርጫ ዝግጅት ወቅት የተለያዩ ጥናቶች እና ስልጠና ሲካሄዱ አካል ጉዳተኞችን የማካተት አስፈላጊነት፣
• አካታች የምርጫ ህግና ፓሊሲ ማአቀፎች አስፈላጊነት፣
• የምርጫ ሥፍራዎች አመቺነት፣ በምርጫ ታዛቢነት መካፈል፣ እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት በምርጫ ሂደት እና ያላቸውን ተሞክሮ መዳሰስ ይገኙበታል።

 

Share this post