Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ከአውሮፓ ህብረት ተወካይና የህብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል

ግንቦት 15 ቀን 2011 ዓ.ም.            

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ ዛሬ ከአውሮፓ ህብረት ተወካይና የህብረቱ አባል አገራት አምባሳደሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም ወቅት የምርጫ ቦርድን አዲስ አደረጃጀት፣ የምርጫ ቦርዱን አዳዲስ የቦርድ አባላት ምልመላ፣ የምርጫ በጀትና የፋይናንስ ድጋፍ፣ የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ህዝበውሳኔ፣ የቤትና የሕዝብ ቆጠራ መራዘም እና ከምርጫ ጋር ያለውን ግንኙነት፣ የተፈናቀሉ ዜጎች እና የመምረጥ መብቶቻቸውን፣ የሴቶችን የምርጫ ተሳትፎ የመሳሰሉት ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሮቹ ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል፡፡ በውይይቱም የአውሮፓ ህብረትም ሆነ የህብረቱ አባል አገራት ቦርዱን ተአማኒ እና ብቃት ያለው ተቋም ለማድረግና መጪው ምርጫ አለም አቀፍ ደረጃ የጠበቀ እንዲሆን የሚደረገውን ጥረት ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል፡፡

Share this post