Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎች የተሣተፉበት የክርክር እና የጥያቄና መልስ መድረክ አካሄደ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተማሪዎች የተሣተፉበት የክርክር እና የጥያቄና መልስ መድረክ ባሳለፍው ሣምንት መጠናቀቂያ ላይ አካሄደ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተካሄደውን የክርክር መድረክ በንግግር የከፈቱት የቦርድ ሥራ አመራር አባሉ ተክሊት ይመስል ሲሆኑ፤ በንግግራቸውም ወጣቶችን ያሣተፈ መሰል መድረክ መዘጋጀቱ ወጣቶች በሀገሪቱ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንዲሁም በማኅበረሰብ ጉዳዮች ንቁ ተሣትፎ እንዲያደርጉ የሚያበረታታና ግንዛቤ የሚፈጥር እንደሆነና ወደፊትም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተናግረዋል።

የቦርዱ የሥነ ዜጋ እና የመራጮች ትምህርት ሥራ ክፍል ያስተባበረው በኢትዮጵያ የምርጫ ሥርዓት ዙሪያ ትኩረት ያደረገው ክርክር እንዲሁም በልዩ ሁኔታ የተካሄደው ጥያቄና መልስ ላይ የተሣተፉ ተከራካሪ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና ክርክሩን የታደሙ ተማሪዎች የክርክር መድረኩ ዜጎች በዕውቀት ላይ የተመሠረተ የምርጫ ተሳትፎ እንዲኖራቸው አስተዋፅዖ እንዳለው ተናግረዋል።

Share this post