Skip to main content

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ታዛቢዎች በሥርዓተ-ፆታ እና አካታችነት እንዲሁም በምርጫ ወቅት ሊፈጸሙ ስለሚችሉ ጥቃቶች አስመልክቶ ሥልጠና ሰጠ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ምርጫ መታዘብ ላይ ለተሠማሩ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በሥርዓተ-ፆታ እና አካታችነት እንዲሁም በምርጫ ወቅት ሊፈጸሙ የሚችሉ ጥቃቶችን አስመልክቶ ሥልጠና ሰጠ።

ለ43 የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች የተሰጠው ሥልጠና በዋናነት ትኩረቱን ያደረገው በሥርዓተ-ፆታ ዕኩልነትና ማኅበራዊ አካታችነት እንዲሁም በምርጫ ወቅት በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንዴት ባለ ሁኔታ መለየትና በተገቢውን መንገድ በትዝብት ሪፖርቱ ውስጥ ማካተት እንደሚቻል የሚያስገነዝብ ሲሆን፤ በተጨማሪም በቦርዱ በሴቶች ላይ የሚደርሱ የሥነ-ልቦና፣ የአካል እና የዲጂታል ጥቃቶችን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲሁም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እየተዘጋጀ ስላለው የጋራ የአሠራር መመሪያ እና የባለድርሻ አካላት ልየታን አስመልክቶ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ቦርዱ ከተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ድርጅት (UN women) ጋር በመተባበር ያካሄደው ይኽ ሥልጠና፤ ቦርዱ የሴቶችና የአካል ጉዳተኞችን ተሣትፎ ከፍ ለማድረግና የሚያጋጥሟቸውንም ተግዳሮቶች መፍትሔ ለመስጠት ከሚሠራቸው በርካታ ሥራዎች ውስጥ አንዱ ነው።

Share this post